She Gave Birth To The World’s First Surviving Septuplets, They Have Turned 18 Now

Aside


በ1997 እኤአ የ29 ዓመት ወጣት የነበረችው ቦቢ ምካግሄይ ከ40 በሚበልጡ ስፔሻሊስቶች ታግዛ ሰባት በህይወት ያሉ ህፃናት በሰላም በመገላገል አለምን ጉድ አሰነች . . . ዜናውም የአለም መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን ተቆጣጠረ

ነ.jpg

In the fall of 1997 a quiet Iowa seamstress made history. Continue reading

Advertisements

ማስታወሻ

Aside


mqdefaultማስታወሻ በተሰኘውና በደራሲ ዘነበ ወላ ተዘጋጅቶ ለህትመት በበቃው የጋሽ ስብሃት ለአብ ገብረ እግዚአብሔርን የህይወት ልምድና ክህሎት በመዘገበበት መፅሃፍ የሽፋን ገጽ ላይ ደራሲ ስብሃት እንዲህ የሚል ፅሁፍ አውጥቶ ነበር (ዋናው ኮፒ በእጅ የተፃፈው በውስጥ ገጽ ዋቢ ሆኖ ታትሟል)፡፡
“ አንባብያን ሆይ!
በልጅነቴ ለመጀመሪያ ግዜ ፎቶ ተነስቼ ሲያሳዩኝ “ይህን ነው የምመስለው?!” ብዬ ገረመኝ። ፎቶውን ግን አምኜዋለሁ። ሌሎችን አንስቶ አይቼዋለሁዋ! ከውጭ ሲያዩኝ ይህን ነው ‘ምመስለው።
ሌላ ቀን ደሞ ድምጼን በቴፕ ሰማሁትና አሁንም ገረመኝ። ስናገር እኔ የምሰማው ሌላ፣ የቴፑ ድምጽ ሌላ!
ዘመናት አለፉ (ቀን መቁጠሪያው ግን አመታት አለፉ ይላል)እኔም ሆንኩ ዘነበ ይህ የምታነቡት መጽሀፍ ገና በሀሳባችን እንኳ ሳይመጣ፣ እሱ ስለ ህይወትና ስነ ጽሁፍ እንዳወራለት ሁኔታዎችን አመቻቸ።
ስናወራ . . . ስናወራ . . . ስናወራ . . . ሳናስበው ይህ መጽሀፍ ብቅ ማለት ጀመረ። ተናገርኩ፣ መዘገበ፣ ጻፈ። በስድሳ አምስት አመት እድሜዬ ይሄ ዘነበ በሚከተሉት ምዕራፎች እንደምታነቡት በቃላት ፎቶ አንስቶኝ አየሁ። ለካ በደግ አይን ሲያዩኝ ይህን እመስላለሁ?! ገርሞኝም አላባራ! Continue reading

ሻካራ እጆች


የአንድ ኩባንያ ባለቤት ለደርጅቱ ብቁ የሆነ ሥራ አስኪያጅ ለመቅጠር ማስታወቂያ አወጣ፡፡ ላወጣው ማስታወቂያ ባቀረቡት ማስረጃ ተወዳድረው ካለፉት ሦስት ሰዎች መካከል በዕድሜ ትንሽ የሆነውን ለቃለ መጠይቅ ጠራው፡፡
ወጣቱ በተጠራበት ቀን አለባበሱን አሳምሮ መንፈሱንም አንቅቶ ጠበቀ፡፡ የኩባንያው ባለቤት የወጣቱን የትምህርት እና የሥራ ሁኔታ የሚገልጠውን መረጃ አገላብጦ አየው፡፡ የተማረው በሀገሪቱ ውስጥ አንቱ በሚባሉ ት/ቤቶች ነው፡፡ የመጀመርያ እና ሁለተኛ ዲግሪውን የሠራው እጅግ በጣም ሀብታሞች በሚማሩባቸው ኮሌጆች ውስጥ ነው፡፡ ያገኛቸው ውጤቶች ምርጥ ከሚባሉት ውጤቶች ውስጥ ናቸው፡፡ በየደረጃው ከነበሩ መምህራን እና የትምህርት ባለሞያዎች ሽልማቶችን እና ማበረታቻዎችን አግኝቷል፡፡
የኩባንያው ባለቤት «ይህንን ሁሉ የትምህርት ክፍያ ይከፍልልህ የነበረው አባትህ ነው)» ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም «አይደለም፤ አባቴን በልጅነቴ ነው ያጣሁት» ሲል መለሰለት፡፡ «ኦ ይቅርታ፤ ታድያ ስኮላርሺፕ አግኝተህ ነበር)» አለው፡፡
«እስካሁን በትምህርት ጉዞዬ ስኮላርሺፕ የሚባል አላጋጠመኝም» ብሎ ፈገግ አለ፡፡
«መቼም ከዘመዶችህ አንዱ የተሻለ ገቢ ያለው ሰው መሆን አለበት)» አለና የኩባንያው ባለቤትም ፈገግታውን በፈገግታ መለሰለት፡፡
«እኔ ሀብታም ዘመድ የለኝም፤ ኧረ እንዲያውም ዘመድ ራሱ የለኝም» አለው ወጣቱ፡፡
የኩባንያው ባለቤት እየተገረመ «ታድያ ይህንን በመሰሉ ት/ቤቶች ገብቶ ለመማር እኮ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል፤ ማን እየከፈለልህ ነበር የምትማረው)» ሲል በአግራሞት ጠየቀው፡፡
«የምትከፍልልኝ እናቴ ነበረች» አለና ወጣቱ በኩራት መለሰ፡፡
«እናትህ ምን ዓይነት ሥራ ነው የምትሠራው)» አለው ባለቤቱ፡፡
«እናቴ የሰዎችን ልብስ እየሰበሰበች የምታጥብ ሴት ናት» አለው ወጣቱ፡፡
«ልብስ እያጠበች ነው አንተን ይህንን በመሳሰሉ ት/ቤቶች ያስተማረችህ)»
«አዎ»
«አንድ ጊዜ እጅህን ለማዬት እችላለሁ» አለው የኩባንያው ባለቤት፡፡ ወጣቱ እጁን ወደ ባለቤቱ ላከው፡፡ እጁ ከኬክ የለሰለሰ ነበረ፡፡
«ለመሆኑ እናትህን በልብስ አጠባው ረድተሃት ታውቃለህ)»
«አላውቅም»
«ለምን)» Continue reading