She Gave Birth To The World’s First Surviving Septuplets, They Have Turned 18 Now

Aside


በ1997 እኤአ የ29 ዓመት ወጣት የነበረችው ቦቢ ምካግሄይ ከ40 በሚበልጡ ስፔሻሊስቶች ታግዛ ሰባት በህይወት ያሉ ህፃናት በሰላም በመገላገል አለምን ጉድ አሰነች . . . ዜናውም የአለም መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን ተቆጣጠረ

ነ.jpg

In the fall of 1997 a quiet Iowa seamstress made history. Continue reading

Advertisements

ፓሪስ ለተሸከርካሪዎች አዲስ የህዝብ ትራንስፖርት ህግ አወጣች

Aside


የፈረንሳይ ዋና ከተማ የሆነችው ፓሪስ ለተሸከርካሪዎች አዲስ የህዝብ ትራንስፖርት ህግ አወጣች፡፡ ህጉም ሙሉ እና ጎዶሎ የሰሌዳ ቁጥር ያላቸውን ተሸከርካሪዎች በፈረቃ በማስተናገድ  የከተማዋን ዋና ጎዳናዎች መጨናነቅ በማርገብ በከተማዋ እየጨመረ ላለው የአየር ብክለትና በጭጋግ መታፈን መልስ ለመስጠት ነው ተብሏል፡፡

CzABRbVXEAAVoOT.jpgParis has introduced the odd-even car rule, and made public transportation in the city and suburbs free in response to the thick “lid of pollution” and smog that is covering the city, the Guardian reported. The city’s electric cars, bike sharing services, metro and buses were made free on Tuesday (December 6), and only cars with even-numbered registration plates were allowed on the roads, with a €22 fine for anyone who broke the rule. Odd numbered cars were allowed on Wednesday, with cars with even-numbered plates back on Thursday.

The car rule has only been introduced four times in the last two decades and never for two consecutive days or longer, according to the Guardian. The Washington Post added that the rule has previously been introduced to deal with higher pollution levels in 2015, 2014 and 1997.

For further reference Click here

ለሀገር አቋራጭ የህዝብ መጓጓዣ አውቶብሶች የኤሌክትሮኒክስ ትኬት ሽያጭ ተጀመረ

Aside


የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የሀገር አቋራጭ የህዝብ መጓጓዣ አውቶብስ ትኬቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስከፈል ጀመረ።

ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ትኬቶቹ በአምስቱም መናኸሪያዎች ወደ የትኛውም ቦታ ከማንኛውም የአውቶብስ ማህበር ለመግዛት የሚያስችሉ ናቸው።

በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ለሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብስ ተገልጋዮች በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የክፍያ አገልግሎት በመዘርጋት የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት ፍሰቱ የተሳካ እንዲሆን ይረዳል። እንዲሁም ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም አቶ ይግዛው ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በአምስቱም መናኸሪያዎች የተጀመረው የኤሌክትሮኒክስ ትኬት ሽያጭ በቀጣይ በ35 የለሁሉ ማእከላትና በ100 ወኪል ኩባንያዎች እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

በቅርቡም በክልል ዋና ከተሞችም የሚተገበር መሆኑን ነው አቶ ይግዛው የገለጹት። ኤፍ.ቢ.ሲ/fbc

 

ፍ/ቤቱ እነ ሃብታሙ አያሌውን ከክስ ነፃ አደረጋቸው

Aside


በከፍተኛ ፍ/ቤት ከቀረበባቸው የሽብር ክስ በነፃ ከተሰናበቱ በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ከጠየቀባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል ሃብታሙ አያሌውን ጨምሮ ሶስቱ በነፃ የተሠናበቱ ሲሆን ሁለቱ ተከላከሉ ተብለዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራር አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ መሆኑን በመግለፅ የተጣለባቸው የጉዞ እገዳ ተነስቶ ወደ ውጭ ሃገር ሄደው እንዲታኩመ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ የነበረ ቢሆንም አዎንታዊ ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
የጠቅላይ ፍ/ቤት ሠበር ሠሚ ችሎት ትናንት በሠጠው ብይን፣ አቶ ሃብታሙ የተጣለባቸው እገዳ መነሣቱንና ከቀረበባቸው ክስም ነፃ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

ይግባኝ ተጠይቆባቸው ከነበሩ የተቃዋሚ አመራሮች መካከል የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሠፋን ጨምሮ የፓርቲ አባል ያልሆኑት አቶ አብርሃም ሠለሞን ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በነፃ ያሠናበታቸው ሲሆን የአረና አመራር አባሉና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አብርሃ ደስታ እንዲሁም የቀድሞ የ‹‹አንድነት›› የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ የነበሩትና በቅርቡ በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የቀረበባቸውን የሽብር ክስ መከላከል ያስፈልጋቸዋል ተብለዋል፡፡

በፍ/ቤቱ ውሳኔ ላይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የተከሳሾቹ የህግ አማካሪና ጠበቃ አመሀ መኮንን፤ ተከላከሉ የተባሉት አቶ አብርሃ ደስታና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ጉዳያቸው ቀድሞ ወደነበረው የከፍተኛው ፍ/ቤት እንደሚመለስ ጠቁመው፤ በቀረበባቸው ክስ ላይ መከላከያ ማስረጃ በማቅረብ ክርክራቸውን እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል፡፡

የፀረ ሽብር አዋጁ በማንኛውም ሁኔታ የዋስ መብት እንደማይፈቅድ የገለፁት አቶ አመሃ፤ የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ተከላከሉ የተባሉ በድጋሚ በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሊከታተሉ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አቃቤ ህግ ወደ ከፍተኛው ፍ/ቤት በመሄድ ተዘግቶ የነበረውን መዝገብ በድጋሚ እንደሚያንቀሳቅስና መጥሪያ ሲደርሳቸው ፍ/ቤት እንደሚቀርቡ አቶ አመሃ አብራርተዋል፡፡
በህመም ላይ የሚገኙት አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት የጉዞ እገዳ እንደሌለባቸውና ወደ ውጭ አገር ሄደው መታከም እንደሚችሉ ታውቋል፡፡

የኡጋንዳው ጳጳስ፤ ሴቶች ወንዶችን መደብደብ እንዲያቆሙ ጠየቁ

Aside


የኡጋንዳው ጳጳስ፤ ሴቶች ወንዶችን መደብደብ እንዲያቆሙ ጠየቁ
ሴቪኒ በበኩላቸው፤ ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡ ወንዶችን አውግዘዋል

የኡጋንዳ ርዕሰ መዲና ካምፓላ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ኪዚቶ ሉዋንግዋ፤የአገሪቱ ሴቶች በወንዶች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡e28b2ffe7bc8b597af9878010b345a09_xl-696x387

ሚፒንጊ በተባለቺው የአገሪቱ አውራጃ ከሚቀርቡ አስር የቤት ውስጥ ጥቃት አቤቱታዎች መካከል ግማሹ፣ በሚስቶቻቸው የተደበደቡ ባሎች ጉዳይ መሆኑን የአገሪቱ ፖሊስ ሪፖርት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው ጳጳሱ፣”ሴቶች ወንዶችን መደብደብ ያቁሙ” ሲሉ መልዕክት ያስተላለፉት ብሏል – ዴይሊ ሞኒተር፡፡ ጳጳሱ አክለውም፣”ወንዶች የቤተሰብ መሪ (ሃላፊ) እንደሆኑ አምነው መቀበል አለባቸው፤ ባሎቻቸውን መውደድና ማክበርም ይጠበቅባቸዋል” ሲሉ መናገራቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

በአንጻሩ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩሪ ሙሴቬኒ ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችል አዲስ ዘመቻ መጀመራቸውን የጠቆመው ዘገባው፤መንግስታቸው ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡ ባሎችን እንደሚያወግዝ ማስታወቃቸውን አመልክቷል፡፡

More at . . . News.et

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስተዳደሩን በተሻለ መምራት የሚችሉ አዲስ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ሾመ።


የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስተዳደሩን በተሻለ መምራት የሚችሉ አዲስ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ሾመ።

የከተማው ምክር ቤት ለሦስት ቀናት ባካሄደው 4ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ሹመቶችን ከመስጠት ባለፈ ዕቅዶችን ገምግሞ አጽድቋል።

f219eeb65c73ecef5cf0eea83bba7fd1_l

በዚህም የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አየነው በላይ ለከተማዋ በከንቲባነት ተሹመዋል።

የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ክብረት ሙሀመድ ምክትል ከንቲባ፤ ቀደም ሲል በምክትል ከንቲባነት ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ምትኩ አለማየሁም ባሉበት አንዲቀጥሉ ምክር ቤቱ አጽድቋል።

የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብይ ኃይሉ እንደገለጹት፥ ከንቲባዎቹ የተሾሙት ያላቸውን የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድና ሕዝባዊ ወገንተኝነታቸውን መሰረት በማድረግ ነው።

ምክር ቤቱ ከሹመቱ በተጨማሪ የ2009 የፊዚካልና የፋይናስ እቅዶችን በጥልቀት ገምግሞ ማጽደቁን የገለጹት አቶ አብይ፥ የከተማውን ወረዳ ፍርድ ቤትና የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እቅዶችንም በመገምገም ማጽደቁን ተናግረዋል።

ዕቅዶቹ የህዝቡን ጥያቄ መፍታት የሚያስችሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ያካተቱ መሆናቸውንም አብራርተዋል።

በተለይ በጥቃቅንና አነስተኛ የሚስተዋሉ የሥራ እጥነት ችግሮችን ለመፍታት በዚህ ዓመት ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን ተናግረዋል።

አቶ አብይ አያይዘው እንደገለጹት፣ ዘንድሮ ከባህር ዳር ከተማ ወደ ኤርፖርት የሚወስደውን የአስፓልት መንገድ የማስፋት ሥራ ለማከናወን ዕቅድ ተይዟል።

በከተማዋ እየተስተዋለ ያለው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሕዝቡ ሰላሙን በማስጠበቅ የራሱን ሚና መወጣት በሚችልበት መንገድ ላይ ምክር ቤቱ መወያየቱንና አቅጣጫ ማስቀመጡንም ኃላፊው ተናግረዋል።

ከህዳር 17 እስከ 19 ቀን 2009 የተካሄደው የከተማው ምክር ቤቱ ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።

የባህር ዳር ከተማ የቀድሞው ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ለክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ መሾማቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

(በእውቀቱ ሥዩም)


ትናንትና ማታ
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡

ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡

ፍቅር በተባለ፤ ግራ- ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡
(በእውቀቱ ሥዩም)

ቦቲዬን አጥቤ በሬ ላይ ባስጣው . . .


   1. ቦቲዬን አጥቤ በሬ ላይ ባስጣው
   ወዳኝ ነው መስለኝ ተራምዳው አለፍች
   2. እወድሽ ነበረ እንደ ከረሜላ
   ታድያ ምን ያረጋል ሱቃችን ተዘጋ
   3. ሒዳችሁ ንግርዋት መታመሜን ከቶ
   አስዋ ገድየላትም ውሽማ ይዛለች
   4. 5ሳንቲም ያለው አይባልም ደሃ
   አምስት ጨምሮ ያጨሳል ግስላ
   5. እዛ ማዶ ጋራ ምን ይንኮሻኮሻል
   ውሻ አይደለምሁ እኔ ምን ምናገባኝ
   6. የኛ ሰፈር ልጆች በጣም ጨዋ ናችው
   መኪና ሲመጣ ይንጠለጠላሉ
   7. እዛ ማዶ ጋራ ምን ይብለጨለጫል
   ሲስተር ናት መስለኝ ቫዝሊን ተቀባታ
   8. ከቤቴ በላይ ቤት አሰራች አሉኝ
   አይኗን አንዳላየው መነጸር ለብሳለች
   9. እኔ እየወደድኩሽ አንቺ ከጠላሽኝ
   ያበላውሽ ፍርፍር አላርጂክ ይሁንብሽ
   10. ስው ፎንቃ ሲይዘው ምግብ ይዘጋዋል
   የኔ ለየት ይላል ፓንት አለብስም አልኩኝ
   11. የኩባያ ወተት የለውም አረፋ
   የ ሚስቴ ጆሮ ኩክ ይዛቃል ባካፋ
   12. ቆለጤ ተቆርጦ ይሁን ላፍንጫሽ
   እኔ ምን አገባኝ ካሸተተልሽ
   13. እዛ ማዶ ሁኖ በፉጨት ቢጠራኝ
   ከብት መስለኩህ እንዴ አልመጣም አልኩኝ
   14. አይሽ አይሽና ይመጣል እንባዬ
   አንቺ አይደለሽም ወይ አለሚቱ ጫኔ
   15. ትላንትና ማታ ሌባ ጉድ ሰራኝ
   በመስኮት መጣና ፓንቴን ሰረቀኝ
   16. እኔ አልፈልግህም ስትለኝ ሰንብታ
   ሌላ አፍቅሬ ስታይ መጥታ ጠየቀችኝ
   17. እንች ሳሚኝ ብየ ከንፈሬን ብሰጣት
   አትችልም መሰለኝ ለሀጯን ለቀቀችኝ
   18. እኔስ እሄዳለው መንገዱን ጠይቄ
   እስከመቼ ድረስ ታክሲ እጠብቃለሁ
   19. እድልሽ ነው እንጅ የሚያንከራትትሽ
   የአንች ባለንጀሮች እንጨት ይሸጣሉ
   20. የምኖደውን ሰው ባናጣው ምናለ
   ካጣነው በሗላ ስለሚያናድደን

  Haro tube