ለሀገር አቋራጭ የህዝብ መጓጓዣ አውቶብሶች የኤሌክትሮኒክስ ትኬት ሽያጭ ተጀመረ

Aside


የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የሀገር አቋራጭ የህዝብ መጓጓዣ አውቶብስ ትኬቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስከፈል ጀመረ።

ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ትኬቶቹ በአምስቱም መናኸሪያዎች ወደ የትኛውም ቦታ ከማንኛውም የአውቶብስ ማህበር ለመግዛት የሚያስችሉ ናቸው።

በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ለሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብስ ተገልጋዮች በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የክፍያ አገልግሎት በመዘርጋት የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት ፍሰቱ የተሳካ እንዲሆን ይረዳል። እንዲሁም ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም አቶ ይግዛው ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በአምስቱም መናኸሪያዎች የተጀመረው የኤሌክትሮኒክስ ትኬት ሽያጭ በቀጣይ በ35 የለሁሉ ማእከላትና በ100 ወኪል ኩባንያዎች እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

በቅርቡም በክልል ዋና ከተሞችም የሚተገበር መሆኑን ነው አቶ ይግዛው የገለጹት። ኤፍ.ቢ.ሲ/fbc

 

ፍ/ቤቱ እነ ሃብታሙ አያሌውን ከክስ ነፃ አደረጋቸው

Aside


በከፍተኛ ፍ/ቤት ከቀረበባቸው የሽብር ክስ በነፃ ከተሰናበቱ በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ከጠየቀባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል ሃብታሙ አያሌውን ጨምሮ ሶስቱ በነፃ የተሠናበቱ ሲሆን ሁለቱ ተከላከሉ ተብለዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራር አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ መሆኑን በመግለፅ የተጣለባቸው የጉዞ እገዳ ተነስቶ ወደ ውጭ ሃገር ሄደው እንዲታኩመ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ የነበረ ቢሆንም አዎንታዊ ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
የጠቅላይ ፍ/ቤት ሠበር ሠሚ ችሎት ትናንት በሠጠው ብይን፣ አቶ ሃብታሙ የተጣለባቸው እገዳ መነሣቱንና ከቀረበባቸው ክስም ነፃ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

ይግባኝ ተጠይቆባቸው ከነበሩ የተቃዋሚ አመራሮች መካከል የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሠፋን ጨምሮ የፓርቲ አባል ያልሆኑት አቶ አብርሃም ሠለሞን ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በነፃ ያሠናበታቸው ሲሆን የአረና አመራር አባሉና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አብርሃ ደስታ እንዲሁም የቀድሞ የ‹‹አንድነት›› የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ የነበሩትና በቅርቡ በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የቀረበባቸውን የሽብር ክስ መከላከል ያስፈልጋቸዋል ተብለዋል፡፡

በፍ/ቤቱ ውሳኔ ላይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የተከሳሾቹ የህግ አማካሪና ጠበቃ አመሀ መኮንን፤ ተከላከሉ የተባሉት አቶ አብርሃ ደስታና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ጉዳያቸው ቀድሞ ወደነበረው የከፍተኛው ፍ/ቤት እንደሚመለስ ጠቁመው፤ በቀረበባቸው ክስ ላይ መከላከያ ማስረጃ በማቅረብ ክርክራቸውን እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል፡፡

የፀረ ሽብር አዋጁ በማንኛውም ሁኔታ የዋስ መብት እንደማይፈቅድ የገለፁት አቶ አመሃ፤ የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ተከላከሉ የተባሉ በድጋሚ በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሊከታተሉ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አቃቤ ህግ ወደ ከፍተኛው ፍ/ቤት በመሄድ ተዘግቶ የነበረውን መዝገብ በድጋሚ እንደሚያንቀሳቅስና መጥሪያ ሲደርሳቸው ፍ/ቤት እንደሚቀርቡ አቶ አመሃ አብራርተዋል፡፡
በህመም ላይ የሚገኙት አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት የጉዞ እገዳ እንደሌለባቸውና ወደ ውጭ አገር ሄደው መታከም እንደሚችሉ ታውቋል፡፡

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ፡፡

Aside


የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ በዚሁ አስቸኳይ ጉባኤው  የቢሮ ሃላፊዎችን ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የክልሉ ዋና ኦዲተር አዲስ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ ለሹመት ያቀረቧቸው የስራ ሃላፊዎች ድርጅቱ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ያካሄደውን ሰፊ ግምገማ መነሻ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም መሰረት

1/ዶክተር ኢንጂነር ገብረ መስቀል ካህሳይ የትምህርት  ቢሮ  ሃላፊ፣

2/ ዶክተር ተስፋ ሚካኤል ገብረ ዮሐንስ የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ፣

3/ዶክተር ሙሉጌታ ሃጎስ የቴክኒክ ትምህርትና ሙያ ስልጠና ቢሮ ሃላፊ ፣

4/ዶክተር የትምወርቅ ገብረመስቀል የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ፣

5/ዶክተር አትንኩት መዝገቡ በግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ በተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ተጨማሪ የቢሮ ሃላፊ እና

6/ ዶክተር አብረሃ  ኪሮስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ወደ ቢሮ እንዲያድግ በማድረግ ሃላፊ ሆነዋል፡፡

በተጨማሪም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋና ሀጎስ የተሾሙ ሲሆን በምክትል ፕሬዝዳንትነት ደግሞ አቶ አማኑኤል አሰፋ እንዲሁም ለክልሉ ዋና ኦዲተር ዶክተር ረዳኢ በርሄ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ከዚህም ሌላ  የውሃ ሀብት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ገብረ መስቀል ታረቀ ለክልሉ የጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ፣ አቶ ጎይቶም ይብራህ ለወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ፣ ዶክተር ገብረህይወት ገብረእግዚአብሔር ለትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈጸማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኡጋንዳው ጳጳስ፤ ሴቶች ወንዶችን መደብደብ እንዲያቆሙ ጠየቁ

Aside


የኡጋንዳው ጳጳስ፤ ሴቶች ወንዶችን መደብደብ እንዲያቆሙ ጠየቁ
ሴቪኒ በበኩላቸው፤ ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡ ወንዶችን አውግዘዋል

የኡጋንዳ ርዕሰ መዲና ካምፓላ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ኪዚቶ ሉዋንግዋ፤የአገሪቱ ሴቶች በወንዶች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡e28b2ffe7bc8b597af9878010b345a09_xl-696x387

ሚፒንጊ በተባለቺው የአገሪቱ አውራጃ ከሚቀርቡ አስር የቤት ውስጥ ጥቃት አቤቱታዎች መካከል ግማሹ፣ በሚስቶቻቸው የተደበደቡ ባሎች ጉዳይ መሆኑን የአገሪቱ ፖሊስ ሪፖርት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው ጳጳሱ፣”ሴቶች ወንዶችን መደብደብ ያቁሙ” ሲሉ መልዕክት ያስተላለፉት ብሏል – ዴይሊ ሞኒተር፡፡ ጳጳሱ አክለውም፣”ወንዶች የቤተሰብ መሪ (ሃላፊ) እንደሆኑ አምነው መቀበል አለባቸው፤ ባሎቻቸውን መውደድና ማክበርም ይጠበቅባቸዋል” ሲሉ መናገራቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

በአንጻሩ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩሪ ሙሴቬኒ ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችል አዲስ ዘመቻ መጀመራቸውን የጠቆመው ዘገባው፤መንግስታቸው ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡ ባሎችን እንደሚያወግዝ ማስታወቃቸውን አመልክቷል፡፡

More at . . . News.et

Woman Born With No Vagina


Woman Born With No Vagina Hopes To Have Children: BORN DIFFERENT

A young woman who was born without a vagina is speaking out about her condition – and is now hoping to become a mother. Devan Merck was devastated after finding out she had no vagina when she was just 12-years-old. The 23-year-old was diagnosed with Mayer-Rokitansky-Küster-Hauser syndrome meaning she had no vaginal canal, a malformed uterus and no cervix. Surgeons created a ‘man-made’ vagina using skin taken from her bottom – allowing her to have sex and lead a normal life. And now Devan and her husband Trent, from Georgia, USA, are hoping to start a family with the help of a surrogate.