ፍካሬ አድዋ(ስለ አድዋ አጭር ማስታወሻ)


ዛሬ አድዋ ነው የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የልደት ቀን፡፡ አድዋን ሳስብ ብዙ ነገሮችን አስባለሁ . . . የተራራ ጫፎች እንደ ጦር ተስለው  ይታዩኛል፡፡ ድራጎንን ገድሎ ብሩታይትን ከፍርሃት ነፃ ያወጣው ሰይፍ ነጸብራቅ  ምኒልክ መዳፍ ውስጥ ይታየኛል፡፡

አድዋ የነፃነት ቀን እንደሆነ አልጠራጠርም . . . ነጭ ቡጢ በጥቁር መዳፍ የከሸፈበት፣ ብርቱ የንቀት ቋጥኝ የተደረመሰበት፣ አንገት በሃፍረት ከመዘለስ የዳነበት ቦታ እንደሆነ አልዘነጋም፡፡  አድዋ እኮ ግዑዝ ተራራ አይደለም  ገበየሁን ያህል የጦር ሳተና ውጦ ጭጭ ያለ ጨለማ፣የእምየን ትዕግስት ተፈታተነ፣ የባራቴሪን ትዕቢት ትቢያ ያደረገ የነጭን ሴራ የበታተነ ሞገድ ነው፡፡ አድዋ የተራራ ሰንሰለት ብቻ  አይደለም  የጣይቱን የሴትነት ብልሃት ያንጸባረቀ  መስተዋት፣ የባልቻን ያህን ድፍረት ያሰናዳ ፣ የአባ መላን ብልሃት የሸረበ፣ለወገን ሃይል ወኔን ያቀበለ፣የባሻ አውአሎም ምስጢረኛ፣ ጀግኖችን በደም አጥምቆ የሀገር ፍቅር ማተብን ያሳሰረ መንፈስ ነው አድዋ፡፡ አድዋ ለኢትዮጵያውያን በዓል ብቻ አይደለም . . .ሳንባን በኩራት ወጥሮ ደረት የሚያስነፋ አየር፣ አንገትን ከመዘለስ ታድጎ ቀና የሚያደርግ  ምርኩዝም ጭምር ነው፡፡

Read the full article here  Adwa

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s