የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ፡፡


የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ በዚሁ አስቸኳይ ጉባኤው  የቢሮ ሃላፊዎችን ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የክልሉ ዋና ኦዲተር አዲስ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ ለሹመት ያቀረቧቸው የስራ ሃላፊዎች ድርጅቱ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ያካሄደውን ሰፊ ግምገማ መነሻ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም መሰረት

1/ዶክተር ኢንጂነር ገብረ መስቀል ካህሳይ የትምህርት  ቢሮ  ሃላፊ፣

2/ ዶክተር ተስፋ ሚካኤል ገብረ ዮሐንስ የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ፣

3/ዶክተር ሙሉጌታ ሃጎስ የቴክኒክ ትምህርትና ሙያ ስልጠና ቢሮ ሃላፊ ፣

4/ዶክተር የትምወርቅ ገብረመስቀል የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ፣

5/ዶክተር አትንኩት መዝገቡ በግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ በተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ተጨማሪ የቢሮ ሃላፊ እና

6/ ዶክተር አብረሃ  ኪሮስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ወደ ቢሮ እንዲያድግ በማድረግ ሃላፊ ሆነዋል፡፡

በተጨማሪም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋና ሀጎስ የተሾሙ ሲሆን በምክትል ፕሬዝዳንትነት ደግሞ አቶ አማኑኤል አሰፋ እንዲሁም ለክልሉ ዋና ኦዲተር ዶክተር ረዳኢ በርሄ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ከዚህም ሌላ  የውሃ ሀብት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ገብረ መስቀል ታረቀ ለክልሉ የጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ፣ አቶ ጎይቶም ይብራህ ለወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ፣ ዶክተር ገብረህይወት ገብረእግዚአብሔር ለትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈጸማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s