ለሀገር አቋራጭ የህዝብ መጓጓዣ አውቶብሶች የኤሌክትሮኒክስ ትኬት ሽያጭ ተጀመረ


የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የሀገር አቋራጭ የህዝብ መጓጓዣ አውቶብስ ትኬቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስከፈል ጀመረ።

ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ትኬቶቹ በአምስቱም መናኸሪያዎች ወደ የትኛውም ቦታ ከማንኛውም የአውቶብስ ማህበር ለመግዛት የሚያስችሉ ናቸው።

በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ለሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብስ ተገልጋዮች በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የክፍያ አገልግሎት በመዘርጋት የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት ፍሰቱ የተሳካ እንዲሆን ይረዳል። እንዲሁም ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም አቶ ይግዛው ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በአምስቱም መናኸሪያዎች የተጀመረው የኤሌክትሮኒክስ ትኬት ሽያጭ በቀጣይ በ35 የለሁሉ ማእከላትና በ100 ወኪል ኩባንያዎች እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

በቅርቡም በክልል ዋና ከተሞችም የሚተገበር መሆኑን ነው አቶ ይግዛው የገለጹት። ኤፍ.ቢ.ሲ/fbc

 

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s