ሰሜን ኮሪያ ለፊደል ካስትሮ ሞት የ3 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አወጀች


ሰሜን ኮሪያ ለፊደል ካስትሮ ሞት የ3 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አወጀች (News.et)

ሰሜን ኮሪያ በፕሬዝዳቷ ኪም ጆንግ አንደበት ‹‹የቅርብ ወዳጄ እና ኮሚኒስታዊው የጦር መሪነት ተምሳሌቴ›› ብላ ለጠራችውና በ90 ዓመቱ ይህችን ዓለም ለተሰናበተው የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ ከኅዳር 19-21/2009 ዓ.ም (እኤአ ከኖቬምበር 28-30/2016) የሚቆይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን አወጀች፡፡

1480262712-fotorcreated-696x392በእነዚህ 3 የሀዘን ቀናት የሰሜን ኮሪያ ሰንደቅ ዓላማ በግማሽ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል፡፡ በእዚህም ሰሜን ኮሪያ ለኩባና እና ላረፉት መሪዋ ያላትን ክብርና አብሮነት ትገልጻለች፡፡

የኩባ እና የሰሜን ኮሪያ ወዳጅነት እኤአ ከ1960 ጀምሮ የተመሠረተና በፖለቲካዊ ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቶ ሁሉን አቀፍ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በተለይም ከ1968ቱ የካስትሮ የሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጉብኝት በኋላ የሁለቱ ሀገራት ኮሚኒስት ፓርቲዎች ፖለቲካዊ ግንኙነት ከዲፕሎማሲ አልፎ ወደ የልብ ከልብ ወዳጅነት እንደተሸጋገረ ይነገራል፡፡

ለዚህም ነው የአሁኑ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም የካስትሮን ሕልፈት ተከትሎ ባፈው እሁድ ባደረጉት ንግግር፡-
‹‹ፊደል ካስትሮ የቅርብ ወዳጃችን እና ኮሚኒስታዊው የጦር መሪነት ተምሳሌታችን ነበር፡፡ ለሁለቱ ሀገራት ፓርቲዎች፣ ለመንግሥታዊም ሆነ ለሕዝብ ለሕዝብ ግንኙታችን ማደግ ትልቁን ድርሻ የተወጣ ጀግና መሪ ነበር፡፡ ለሀገራችን መልሶ መዋሐድና ጥንካሬም ካስትሮ የተጫወተው ሚና መቼም የሚረሳ አይደለም››
ሲሉ የገለጹት፡፡

‹‹አብዮት ማለት በትናንት እና በነገ (ባለፈውና በመጪው ጊዜ) መካከል እስከ ሞት ድረስ የሚደረግ ትግል ነው›› – ካስትሮ ከሚታወቁባው ጥቅሶች አንዱ፡፡

ዘገባው የRT.com እና የAFP ነው፡፡

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s