ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአገር አቀፍ ደረጃ 1ኛ ሆነ


n.jpgባሳለፍንው ሳምንት የአፋር ክልል መዲና የሆነችው እና የሠመራ ዩኒቨርሲቲ መገኛዋ ሠመራ አገር አቀፉን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዓመታዊ ጉባኤ አስተናግዳ ነበር፡፡

ጉባኤው የ2008 ዓ.ም. የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች አፈጻጸም የተገመገመበት ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎች በመማር ማስተማር፣ በትምህርት ጥራት፣ በምርምርና ስርጸት፣ በማህበረሰብ አቀፍ ስራዎቻቸው በዓመቱ ያከናወኑትን የአፈጻጸም ተግባር በመገምገም እንደወትሮው ሁሉ ደረጃ ሰጥቷል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አቻው ከሆኑ አንጋፋዎቹ አስር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በተመደበበት ምድብ በአገር አቀፍ ደረጃ አንደኛ ሆኗል፡፡

በማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች በእጅጉ ገኖ የሚጠቀሰው እና ከጎንደር ከተማ ጋር ተነጣጥሎ የማይታየው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋሲል ከነማ ስፖርት ቡድን ግንባር ቀደም አጋር በመሆን ራሱን ከከተማዋ ገጽታ ጋር አስተሳስሮ ሲኖር የቆየ ሲሆን በቅርቡ በቃጠሎ የወደመውን የጎንደር ቅዳሜ ገበያ መልሶ የማልማት ስራ በገንዘብና በሙያ በመደገፍ ዳግም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ልብ የገባ ነው፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሳለፍንው ዓመት የተካሄደውን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት አሸናፊ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ DireTube.com

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s