ታላቁ ሩጫ 2009 በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ ተካሄደ


cc58_XL-696x397.jpgታላቁ ሩጫ 2009 በኢትዮጵያ 42 ሺህ ተወዳዳሪዎችን በማሳተፍ ዛሬ ለ 16ኛ ጊዜ ተካሄደ። መነሻና መድረሻውን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ባደረገው በዚሁ ውድድር 500 ልምድ ያላቸው አትሌቶችና ከ 250 በላይ የውጭ አገር ዜጎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በወንዶች የደብረ ብርሃን ማሰልጠኛ ማዕከል አትሌት የሆነው አቤ ጋሻሁን የ 16ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ሆኗል።
አቤ ውድድሩን ለመጨረስ 28 ደቂቃ 53 ሴኮንድ ከ 80 ማይክሮ ሴኮንድ ፈጅቶበታል።
ኬንያዊው አትሌት ጆረም ኑምባሳ ሁለተኛ እንዲሁም አዱኛ ታከለ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል።
አትሌት አዱኛ ባለፈው ዓመት በታላቁ ሩጫ ሦስተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
በሴቶች ደግሞ ፎቴን ተስፋዬ ከመሰቦ ስፖርት ክለብ በ 33 ደቂቃ ከ 09 ሴኮንድ በመግባት አሸናፊ ሆናለች።
መልዬ ደቀቦ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሁለተኛ እንዲሁም ታደለች በቀለ ከኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
ውድድሩን በአንደኝነት ላጠናቀቁ የ 50 ሺህ፣ ሁለተኛ ለወጡ 25 ሺህ ሶስተኛ ሆነው ላጠናቀቁ ደግሞ የ 10 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አትሌት አቤ ጋሻሁንና አትሌት ፎቴን ተስፋዬ በውደድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ተካፍለው በማሸነፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ውድድሩ በቀጣይ በዓለም አቀፍ መድረኮች በመሳተፍ የአገራቸውን ስም ለማስጠራት ልምድ እንደሚሆናቸው ገልጸዋል።
የታላቁ ሩጫ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ውድድሩን ሠላማዊ በሆነ መንገድ ማጠናቀቁና አዳዲስ አሸናፊዎች መምጣታቸው አስደሳች ነው ብሎታል።
ታላቁ ሩጫ ለአትሌቶች የውድድር ዕድል በመፍጠር ተተኪዎችን እንዲፈሩ እያደረገ መሆኑም አትሌት ኃይሌ ገልጿል።
ዘንድሮ የተሳታፊዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ እንደ ልብ ለመሮጥ አመቺ ባለመሆኑ ችግሩን ለመፍታት ተሳታፊዎችን በሁለት በመክፈል በቀይ ሪቫን 6 ሺህ፣ በአረንጓዴ ደግሞ 36 ሺህ እንዲሮጡ ተደርጓል።
የቀይ ሪቫን ውድድራቸውን ቀድመው የሚጀምሩና 10 ኪሎ ሜትሩን ከአንድ ሰዓት በታች የሚያጠናቅቁ፣ የአረንጋዴ ሪቫን ደግሞ ዘግይተው የሚጀምሩ ውድድሩን ለመጨረስ ከአንድ ሰዓት በላይ የሚወስድባቸው ናቸው።
በውድድሩ አምባሳደሮች፣ ታዋቂ አትሌቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አርቲስቶችና ሌሎች ባለሥልጣናት ተሳትፈዋል።

የአፍሪካ ታላቁ የጎዳና ላይ ሩጫ የሆነው ታላቁ ሩጫ ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር “መኖር ለዚህ አበቃኝ” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።
ENA
News Net

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s