አሊ ቢራ


df1f275fce9840e9bc283962969870e8አሊ ቢራ ታዋቂ የኦሮምኛ ቇንቇ ዘፋኝሢሆኑ በሙዚቃው ሙያ ለሃምሣ አመታት ላበረከቱት አሥተዋፅኦም ከጅማ ዩኒቨርሥቲ የክብር
ዶክትሬት ተሸላሚ ለመሆን የበቁ ናቸው። በግንቦት18 ቀን1940 አመተ ምህረት በድሬዳዋ ከተማ የተወለዱት አሊ ቢራ እናት እና አባታ
ቸው ያወጡላቸው ሥም አሊ መሐመድ ሙሳ ይባላል። መጀመሪያ በዘፈኑት ዘፈን የተነሣ ነው አሊ ቢራ የሚለው መጠሪያ
የተሠጣቸው። አሊ ቢራ የመጀመሪያ ትምህርታቸውን
በመድረስ ጅዲዳ እና በልዑል መኮንን ትምህርት ቤት እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ወደአዲስ አበባ በመሄድ በካቴድራል
ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። አመሪካን አገር በሚገኘው የሳንታ ሞኒካ ኮሌጅም የሙዚቃ ትምህርት እንደተከታተሉ ተፅፎላቸዋል።
አሊ ቢራ ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ መዝፈን የጀመሩት 15 አመታቸው ማለትም በ1955 ድሬዳዋ ውሥጥ በነበረው አፈረን ቀሎ ተብሎ በሚጠራ ባንድ ውሥጥ አጃቢ ዘፋኝ በመሆን ነው።
ከዚያም በክቡር ዘበኛ ኦርኬሥትራ ተቀትረው ለሦሥት አመታት ተጫውተዋል። ችሎታቸው እየጎለበተ ሢሄድም አይቤክሥ ባንድን
በመቀላቀል ለሥምንት አመታት የሙዚቃ ሥራወቻቸውን  በዲ-አፍሪክ ሢያቀርቡ ቆይተዋል። አሊ ቢራ በአጠቃላይ 264
ዘፈኖችን የተጫወቱ ሢሆን ያሣተሟቸው ካሤት ቁጥር ግን ሥድሥት ብቻ ነው።  አሊ ቢራ  በዘፈናቸው  ለፖለቲካዊ  ጉዳይ
የበለ ጠ  ትኩረት  ይሰጡ  እንደነበር  ሎሚ  ለተባለ  መፅሄት  በተደረገላቸው  ቃለ  መጠይቅ  ላይ  ተናግረዋል ።
በዚሁ  ጉዳይ  አሥመልክተዉም  የሚከተለውን  እንዳሉ  “ታሪ ካዊ  መዝገበ  ሠብ   በሚለው  መፅሃፍ  ላይ ተጠቅሧል።

“በቇንቇችን ላይ የነበረው ጫና ትንሽ የበዛ ነበር። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ግን ደግሞ ኦሮሞ ነኝ። የነበረው ስርዐት ግን ይሄን አይቀበለውም። ክሌሎች በተለየ ኦሮሞ
እና ኦሮምኛ ቇንቇ ላይ የተለየ ተፅኖ ነበረው። ሥለዚህ በወቅቱ የነበርውን ነገርበመንቀፍ እዘፍን ነበር”
አሊ ቢራ ከመዝፈንም ባሻገር  ፒያኖ ፣  ጊታር ፣  እና  ኡድ የተባሉ  የሙዚቃ  መሣሪያዎችን እንደሚጫዎቱ
ታውቇል። ሥምንት ያክል ቇንቇዎችንም እንደሚናገሩ በተላያየ መጣጥፎች እና ቃለ መጠይቆች ተዘግቧል።
ከነዚህም ውስጥ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ሶማሊኛ፣ አፋርኛ፣ ሃረሪኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ በዋናነት ይተቀሣሉ። አሊ ቢራ
የሃምሣ አመት የሙዚቃ ህይዎት የወርቅ እዮቤልዮ ” መማር አሁንም መማር” በሚል መሪ መፈክር
በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል። አሊ ቢራ በቅርብ ጊዜ ጭንቅላታቸው ላይ በበቀለ እጢ ምክንያት የግራ አይናቸው ማየት እንዳቆመ እና
 የቀኙም እንደተዳከመ ተገልፇል። እግራቸውም በካንሠር ተጠቅቶ በቀዶ ጥገና ህክምና እንደዳኑ ታውቇል።

ምንጭ:
– ታሪካዊ መዝገበ ሠብ መፅሃፍ
– ሎሚ መፅሄት
– ሠንደቅ ጋዜጣ
http://www.sewasew.com/phrases/1026?withDetails=1

please enter a message