ታላቁ እስክንድርን ባልሆን ኖሮ ዲዎጋንን መሆን እመርጥ ነበር!


download-1

ጠቢቡ ዲዎጋን -ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው በ‹‹ቡክ ፎር ኦል›› ገጽ

ግሪክ ውስጥ፡ ቆሮንጦስ በሚባል ቦታ ይኖር የነበረ ዲዎጋን የሚባል አንድ ጠቢብ ሰው ነበር። እሱን ለማየትና ሲናገር ለመስማት ከሩቅ ቦታ ድረስ ጭምር፡ የሚመጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ። የጠበቢነቱን ያክል ግን አንዳንድ እንግዳና ያልተለመዱ ባህሪዎች ነበሩት። አንድ ሰው ከሚያስፈልገው በላይ የሆነ ንብረት ሊኖረው አይገባም፡ የሰው ልጅም ትንሽ ንብረት በቂው ነው ብሎ ያምን ነበር።በዚህም የተነሳ ቤት አልነበረውም— በርሜል ወይም ገንዳ ውስጥ ይተኛ ነበር።ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስም በርሜሉን እየገፋ ይወስድ ነበር።
ቀኑንም የሚያሳልፈው፡ በአደባባይ ተቀምጦ፡ እሱን ለመስማት ለተሰበሰቡ ሁሉ ጥበቡን በማካፈል ነበር። አንድ ቀን፡ በጠራራ ጸሀይ፡ ዲዎጋን ፋኖሱን ለኩሶ፡ በጎዳናው እየተዘዋወረ፡ ልክ አንድ ነገር ጠፍቶበት፡ የሚፈልግ መሰለ።download

”በቀን ብርሀን፡ ለምን ፋኖስህን ለኩሰህ ትዞራለህ?“ ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቀው
”ቅን የሆነ ሰው እየፈለግኩኝ ነው“ ብሎ መለሰ። ታላቁ እስክንድር አለምን በሙሉ እየተቆጣጠረ፡ ቆሮንጦስ ሲደርስ፡ እሱን ለማየትና ለማመስገን ሁሉም ሰው ተሰበሰበ፤ ዲዎጋን ግን አልመጣም። ታላቁ እስክንድር ለማየት የፈለገው ግን አንድ ዲዎጋንን ብቻ ነበር።
ስለዚህ ጠቢቡ ወደ ንጉሱ ስላልመጣ፡ ንጉሱ ወደ ጠቢቡ ሄደ።ዲዎጋንንም ከመንገድ በጣም የራቀ ቦታ ላይ፡ ከበርሜሉ አጠገብ ተጋድሞ ጸሀይ ሲሞቅ አገኘው።
ንጉሱ ከኋላው በጣም ብዙ ሰው አስከትሎ ሲመጣ ያየው ዲዎጋን ከተጋደመበት ቀና ብሎ እስክንድርን ተመለከተ።እስክንድርም ሰላምታ ካቀረበለት በኋላ እንዲህ አለው፦
”ዲዎጋን!ስላንተ ጥበብ ብዙ ሰምቻለሁ። የማደርግልህ ነገር ይኖራል?“”አዎ“ አለ ዲዎጋን” ጸሀይዋን ስለጋረድከኝ ወደ ጎን ዞር በልልኝ“ ንጉሱ ያልጠበቀው መልስ ስለነበር በጣም ተደነቀ።ይሁን እንጂ በመልሱ አልተናደደም፤ ይልቁንም ለዚህ እንግዳ ሰው ያለው አድናቆት ጨመረ። ፊቱን አዙሮ ሲመለስም፡ ለጦር አለቆቹ እንዲህ አላቸው፦”ታላቁ እስክንድርን ባልሆን ኖሮ ዲዎጋንን መሆን እመርጥ ነበር!“
(ዲዎጋን፡ cynicism ተብሎ ከሚታወቀው የፍልስፍና ጽንሰ ሀሳብ መስራቾች አንዱ ሲሆን፡ ይህንን መርሁንም በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ጭምር ኖሮ አሳይቷል። እንደ cynics ከሆነ፡ የሰው ልጅ ቀላልና ያልተወሳሰበ፡ ከተፈጥሮም የሚስማማ ተራ ህይወት መኖር አለበት ብለው ያምናሉ።ሀብት፡ እውቅና እና ስልጣንም በcynics ዘንድ “የተከለከሉ ፍሬዎች” ናቸው።በዚህም የሰው ልጆች ደስተኛ ኑሮ ይኖራሉ። በምድር ላይ ያለው ሀብትም፡ የሁሉም የጋራ ንብረት መሆኑንም ያሰምሩበታል።ስቃይና መከራም የሚመነጨው፡ የነገሮችን ትክክለኛ ዋጋ ካለመረዳት መሆኑን ያክሉበታል።ይህም አለመረዳት የሚመጣው፡ ከማህበረሰቡ የተዛባ አመለካከትና ካረጀ፡ካፈጀ ልምድ መሆኑን በማስረዳት ይደመድማሉ።)
Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s