ታሪክና ትምህርት


==========የፌስ ቡክ ገፃችንን https://www.facebook.com/netsawubet ላይክ በማድረግ፣ ፖስቶቻችን ሼር፣ኮሜንት በማድረግና ለጓደኞችዎ በመጋበዝ ሃላፊነትዎን ይወጡ፡ እንዲሁም በብሎግ አድራሻችን http://www.netsawubet.worpress.com/ ገብተው ሊከተሉን ይችላሉ፡፡========

562473_388324301204440_84722010_nአሁን አሁን በየአካባቢያችን የምናየው የአለባበስ፣ የአመጋገብና የአነጋገር ሁኔታ ከዋናውና ነባሩ (ያልተበረዘው) ኢትዮጵያዊ የአኗኗር ዘይቤያችንና ባህላችን ጋር በእጅጉ እያፈነገጠና ምዕራባዊ እየሆነ መምጣቱ የሰነባበተና ፀሃይ የሞቀው ጉዳይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህንን በተለይ አለባበሱንና የቋንቋ አጠቃቀማችንን በተመለከተ ብዙ ዓይነት ሃሳቦች የሚሰነዘሩ ቢሆንም በዋናነት ግን ሁለት ጎራዎች አሉ፡፡ እነሱም ባህል ከዘመን ጋር የሚለዋወጥና የሚያድግ የሚሻሻል ማህበራዊ ሁነት ነው ስለዚህም አሁን የሚታየው የአነጋገርና የአለባበስ ስርዓት(ስርዓት እንኳን አልለውም!) ሊነቀፍና ሊወገዝ አይገባውም የሚልና ሁለተኛው ደግሞ በፍጹም ይህ የእኛን ወግ ባህልና ልማድ የሚያጠፋና የእኛ መገለጫ መሆን የሌለበት ነው ብለው የሚከራከሩ አሉ፡፡ ለማንኛውም ይህንን ርዕስ በየራሳችሁ አስቡበትና . . . ለልጆቻችን፣ ጓደኞቻችንና በዙሪያችን ላሉት ሰዎች እንዴት ነው ባህላቸውን እንዲያውቁና እንዲጠብቁ እያስተማርናቸው ያለን; የሚለው ነገር ላይ ላተኩር፡፡ ብዙ ሰዎችን በመንገድ ላይም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሳይ በድፍን ከማጥላላትና ከመሳደብ ውጭ ለማስተማርና ለመምከር የሚርት እምብዛም አያጋጥመኝም አስተማርን፣ መከርን ካሉም ስድብና ነቀፋ ይቀናቸዋል፡ ነገር ግን ምክራችን ውጤት ያመጣ ዘንድ የምንመክራቸው ሰዎች በቅርብ መቢያውቁትና ሁሌ ሊያስታውሱት በሚችሉት መንገድ መሆን አለበት እላለሁ፡፡ ለዚህም ሳነብ ያገኘሁትን ይህንን አስተማሪና ጥበብ የተሞላበት ታሪክ ላካፍላችሁ ወደድኩ፡ ፡
****

ታላቁ የቻይና ንጉስ ቻን ብዙ ግዛቶችን በቁጥጥሩ ውስጥ አስገብቶ ማስገበር ከቻለ በኋላ በጠና ይታመማል፡፡ የመሞቻው ጊዜ መዳረሱን የተረዳው ቻን 12 ወንድ ልጆቹን እንዲጠሩለትና እያንዳንዳቸው ቀስት(ፍላፃ) ይዘው እንዲመጡ ያዝና ልጆቹም እንደታዘዙት ያደርጋሉ፡፡ ልጆቹ ያመጧቸውን ቀስቶች ባየ ጊዜ በአንድ ላይ አድርጎ 3 ቦታ ላይ እንዲያስራቸውና እንዲሰብራቸው አዝዞ ለትልቁ ልጁ ሰጠው፡፡ ከሁሉም ትልቁ የሆነው ልጅም እንደተባለው ፍላፃዎቹን ከ 3ቦታ ላይ ካሰራቸው በኋላ ለመስበር ቢሞክርም አልተቻለውም፡ ከዚያም ሁለተኛው፣ሶስተናው እያሉ ሁሉም ልጆች እንዲሞክሩ እድል ተሰጣቸው ነገር ግን አንዳቸውም እነዛን በአንድ ላይ የታሰሩ ዘንጎች መስበር አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሱ ቻንም ይህንን ከተመለከተ በኋላ ቀስቶቹ የታሰሩበትን ገመድ ፈትቶ እንዲበታትናቸውና ተራ በተራ እንዲሰብራቸው ለትንሹ ልጅ ያዘዋል፡ ታዳጊው ልጅም እንደተባለው ሲያደርግ አንድ በአንድ ሁሉንም ቀስቶች መስበር ቻለ፡፡ ንጉሱም ወደ ልጆቹ በመዞር “ስለምን እነዚህን ዘንጎች መስበር አቃታችሁ;” ሲል ጠየቃቸው ልጆቹም “በህብረት በመታሰራቸው ልንሰብራቸው አልተቻለንም ጥንካሬያችንን ተፈታተኑን” በማለት መለሱለት፡፡ “ስለምን ትንሽ ወንድማችሁ አንድባንድ ሰበራቸው;” ብሎ በድጋሚ ሲጠይቃቸው “አንዳቸው ከአንዳቸው መተባበር ስላልቻሉና ስለተበታተኑ” በማለት መለሱ፡፡ ንጉሱም በልጆቹ አስተዋይነት ተደስቶ “እነዚህ ቀስቶች እናንተ ናችሁ፤ ስለዚህም እናንተ እርስበርሳችሁ በሶስት ነገሮች ማለትም በፍቅር፣በሃቅና በጥሩ ስነ-ምግባር እስከታሰራችሁም እስከተባበራችሁ ድረስ ማንም ስልጣንም ሆነ ክብርን ከናንተ መንጠቅ የሚቻለው የለም፡ ይህንን ማድረግ ከተሳናችሁን መተማመንና መተባበር ከራቃችሁ ግን ደካሞች ትሆናላችሁ” ብሏቸው ሞተ፤ ልጆቹም አባታቸው በሰጣቸው ትምህርትና ምክር እጅጉን ተደነቁ፡፡
Travel
sir John Mendeville (mid 14c)
***
ከዚህ ታሪክ ልንማራቸው የሚገቡን
1. እርስ በርሳችን እስከተዋደድንና መተባበር እስከቻልን ድረስ ያንዳችን ድክመት በሌሎቻችን እየተሞላ ሁሌም ተንካራና ብርቱ መሆን እንደምንችል
2. በጥሩ ስነ-ምግባር እስከታነጽንና ለሰዎች ፍቅርና እንክብካቤን እስካልነፈግን ድረስ ሰላማዊና አስደሳች ህይዎት እንደሚኖረን
3. በዋናነት ደግሞ ሰዎችን ስንመክርና ድክመታቸውን ስንሞላ በቅርብ በሚያውቁትና በቀላሉ ሊገነዘቡት በሚችሉ ምሳሌ መሆን እንዳለበት እንማራለን፡፡
በአጠቃላይ ከታሪኩ ብዙ ቁም ነገሮችን እንዳገኛችሁ አገምታለጉ፡፡

==========የፌስ ቡክ ገፃችንን https://www.facebook.com/netsawubet ላይክ በማድረግ፣ ፖስቶቻችን ሼር፣ኮሜንት በማድረግና ለጓደኞችዎ በመጋበዝ ሃላፊነትዎን ይወጡ፡ እንዲሁም በብሎግ አድራሻችን http://www.netsawubet.worpress.com/ ገብተው ሊከተሉን ይችላሉ፡፡========

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s