ማስታወሻ


mqdefaultማስታወሻ በተሰኘውና በደራሲ ዘነበ ወላ ተዘጋጅቶ ለህትመት በበቃው የጋሽ ስብሃት ለአብ ገብረ እግዚአብሔርን የህይወት ልምድና ክህሎት በመዘገበበት መፅሃፍ የሽፋን ገጽ ላይ ደራሲ ስብሃት እንዲህ የሚል ፅሁፍ አውጥቶ ነበር (ዋናው ኮፒ በእጅ የተፃፈው በውስጥ ገጽ ዋቢ ሆኖ ታትሟል)፡፡
“ አንባብያን ሆይ!
በልጅነቴ ለመጀመሪያ ግዜ ፎቶ ተነስቼ ሲያሳዩኝ “ይህን ነው የምመስለው?!” ብዬ ገረመኝ። ፎቶውን ግን አምኜዋለሁ። ሌሎችን አንስቶ አይቼዋለሁዋ! ከውጭ ሲያዩኝ ይህን ነው ‘ምመስለው።
ሌላ ቀን ደሞ ድምጼን በቴፕ ሰማሁትና አሁንም ገረመኝ። ስናገር እኔ የምሰማው ሌላ፣ የቴፑ ድምጽ ሌላ!
ዘመናት አለፉ (ቀን መቁጠሪያው ግን አመታት አለፉ ይላል)እኔም ሆንኩ ዘነበ ይህ የምታነቡት መጽሀፍ ገና በሀሳባችን እንኳ ሳይመጣ፣ እሱ ስለ ህይወትና ስነ ጽሁፍ እንዳወራለት ሁኔታዎችን አመቻቸ።
ስናወራ . . . ስናወራ . . . ስናወራ . . . ሳናስበው ይህ መጽሀፍ ብቅ ማለት ጀመረ። ተናገርኩ፣ መዘገበ፣ ጻፈ። በስድሳ አምስት አመት እድሜዬ ይሄ ዘነበ በሚከተሉት ምዕራፎች እንደምታነቡት በቃላት ፎቶ አንስቶኝ አየሁ። ለካ በደግ አይን ሲያዩኝ ይህን እመስላለሁ?! ገርሞኝም አላባራ!
አብራችሁኝ ስለ ህይወት ተአምራት እየተገረማችሁ በቃል የተሳለውን ፎቶዬን ታዩ ዘንድ በአክብሮት እጋብዛለሁ።
ዘነበ ወላ ያዘጋጀውን የህይወቴን አልበም እየከፈታችሁ ነው። መልካም እይታ! ለሁሉም ለሁሉም እነሆ በረከት! . . . በመጨረሻም የገረመኝ— የዘነበ ወላ ብእር እንደ ሲኒማ ወለል አድርጎ ያሳየናል።
የዘነበ አገሮች(ጋሞ የሚባሉት) አብሯቸው የሌለውን ፣ የሚያከብሩትና የሚያደንቁትን ሰው ሲያስታውሱት << ኢዚ ባይንታ ሶን ኢዛ ሱንሳ ዴንሳሼ ሀኢካ ኢዛስ ኤቃይስ!>> ይላሉ። ”እሱ በሌለበት ስሙን ሳነሳው፣ ተነስቼ ቆሜ <ኖር!> እያልኩት ነው” እንደ ማለት ነው። በዚያውም ለዘነበ አባትና እናት፣ ለአቶ ወላ ወጋንና ለወይዘሮ ወርቅነሽ ባላ፣ እሱን ወልደው ለሰጡን ወላዬ እና እማዬ (ትእዛዙ የግዜር ቢሆንም) በአክብሮት ተነስተን እጅ እንነሳቸዋለን።
መልካም ንባብ!
ፊርማ
ስብሐት ለአብ
25/6/93”

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s