እናትነት ፈተና ነው!


“ልጄ የዘወትር ምኞቱ የእስራኤልን ክብር ማየት ብቻ ነበር” ትላለች የይሁዳ እናት ሲቦራ ፤
የይሁዳ እናት ሲቦራ እንዲህ ትለናለች፤ “በ17 አመቱ የሮማ ወታደር በጦር እግሩን አቁስሎ ታስሮ ነበር በዛ የወጣትነት እድሜው የአይሁድ ወጣቶችን ልብ ስለነጻነት ሲያነሳሳ ይውል ነበር፤የእስራኤልን ክብር በአደባባይ ይመሰክር ነበር፡፡
ብቸኛው ልጄ እርሱ እንደነበር ታውቁልኝ ዘንድ እወዳለው፡፡ዛሬ እንዲህ ደርቀው የምታይዋቸውን ጡቶቼን ይዞ የጠባ ፤ በአትክልት ስፍራ በትንንሽ ጣቶቹ እጄን ይዞ መሄድ የለመደ ብቸኛው ልጄ ነው፡፡
የመጀመሪያ ብቸኛ ልጄ ነበርና በህይወቱ ውስጥ የሚጨምር እያንዳንዷየእድገት ደረጃ የእኔንም ህይወት ትጨምር ነበር፡፡ማንኛዋም እናት ከወለደች በኋላ የእርምጃዋን ልክ በልጅዋ እርምጃ እንደሚወሰን ሁሉ የእኔም እንደዚያው ነበር፡፡
ልጄን እወደዋለው፤ እስከዘላለምም እወደዋለው፤ ፍቅር ከስጋ ቢሆን ኖሮ ስጋዬን አቃጥዬ በመጣል እገላገል ነበር፤ነገር ግን ከነፍስ ሆነና ልደርስበት አልቻልኩም፡፡
ወደ እየሱስ እናት ሂዱ፤ በእኔ ልብ ያለፈው ልጅ የማጣት ሰይፍ በእሷም ልብ ውስጥ አልፏልና የሚሰማኝን በሚገባ ልትነግራቹ ትችላለች ያን ጊዜም ትረዱኝ ይሆናል፡፡” (ምንጭ የካህሊል ጂብራን የሆነው እየሱስ የሰው ልጅ ከሚለው መጽሃፍ ተርጓሚው ሃይለጊየዮርጊስ ማሞ ነው)፡፡ እንግዲህ እናትነት ፈተና ነው፤ እስቲ ጥያቄ ልጠይቅ፤ ይሁዳ አጥፍቷል ወይስ ጥፋት አልሰራም?? ይሁዳ እየሱስን አሳልፎ ስለሰጠ አጥፍቷል ትላላቹ ወይስ ምድር ከመፈጠሯ በፊት ይሄ እንደሚሆን የታወቀ ስለሆነ ይሁዳ የእግዚያብሄርን ቃል ፈጸመ እንጂ ጥፋት አላጠፋም ትላላቹ?????፡፡Tewodros Tezera

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s