ነፍጠኛው ትውልድ


ይህ የታሪክ ገጽ አዲስ ሆኖ በብዙ አንባብያን ባልታወቀበት ጊዜ የለጠፍኳቸውን ጠቃሚ የሆኖ ታሪካዊ ጦማሮችን በድጋሚ እለጥፋቸዋለሁ ይህንን የነፍጥ እና የነፍጠኛ ታሪክ ከዚህ በፊት ለጥፊ ነፍጥ በኢትዮጲያ ምድር መውዜር ፣ዲሞፍተር፣ ምንሽር፣ ራስ ማስር፣ ፊሻሌ፣ ቤልጅግ ከሚባሉት የጦር መሳሪያወች ቀድማ የገባች የጠብ መንጃ እንደነበረች አስታውሻለሁ እንዲሁም “ብረት ያልታጠቀ ጥሎ ያልወደቀ” ወንድ አይደለም ተብሎ በሚታመንበት እና አልመግባባትን ድርድር ሳይሆን ጦር በሚፈታበት ዘመን በሁሉም የኢትዮጲያ ክልል የኖረው ትውልድ ነፍጥ ከትከሻው ስለማትለየው ነፍጠኛ ይባል ነበር።

በአጤ ምንሊክ ዘመንም ከተለያዩ የኢትዮጲያ ግዛቶች ተመርጠው የተቀጠሩት ዘመናዊ ፖሊሶች ነፍጥ ስለሚያነግቱ እነሱም ነፈጥኞች ይባሉ ነበር፣ ከወለጋ ምድር የሚጠለቁት የጥንቱ ወጌሻ ባሻ ታሲሳ ነፍጥ ስለነበራቸው እሳቸውም ነፍጠኛ ነበሩ, ከትግራይ ምድር የሚጠለቀው ወዴ ሐጎስ ነፍጡን እንደሚስቱ ስለሚወዳት እሱንም ነፍጠኛ ይሉት ነበር።

በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1930 በራስ ተፈሪ እና በራስ ጉግሳ መሀል በዘውድ ሽኩቻ በተፈጠረው ጦርነት ላይ ራስ ጉግሳ ተሸንፈው ከወደቁ በኋላ የተማረኩት ከጎንደር ምድር የሚጠለቁት የጦር መሪያቸው አባ ሹምዬ ተማርኬ ከእንግዲህ የጎንደርን አፈር እግሬ አይረግጠውም ብለው ስለተማጸኑ በጦር ተከበው በነፍጥ ጥይት ናዳ ከአንቸም ጦር ሜዳ ተረሽነዋል።

ነፍጠኛ ማለት ነፍጥ ያነገተ ማለት ነው እንጂ ስድብ መስሎን ነፍጠኛው እያልን ጥሬ አንሁን። ምነው ጎበዝ… በዚህ በሰለጠነ ዘመን ትንሽ ነቃ እንበል እንጂ….3 ሺህ ዘመን ከኋላ? አረ እባካችሁ ጡር ነው።Eduardo’s History Page

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s