ልዑል ራስ መኮንን (አባ ኮራ/ አባ ቃኘው)


abበአጤ ምንሊክ እና የሐረሩ ሹም በራስ መኮንን መካከል የነበረውን ዝምድና ለጠየቃችሁኝ ወዳጆቼ መልስ ይሆን ዘንድ በአለኝ መረጃ መሰረት በሁለቱ መሪወች መካከል የነበረው የስጋ ሳይሆን የጋብቻ ዝምድና ነበር, እንዲሁም ከልጅነት እስከእለት ዕልፈት ሳይለያዩ በመኖራቸው እና መወለደም ቋንቋ በመሆኑ ራስ መኮንን የአጤ ምንሊክ ታናሽ ወንድም ነበሩ በማለት ብዙ የታሪክ ጦማሪወች ጽፈዋል።

ከሸዋ ምድር የሚጠለቁት በመዕራባውያን አቆጣጠጠር በ1852 አንኮብር ጎራ ላይ ተወልደው ሐረርን ለ16 አመታት ያስተዳደሩት እና ከአደዋ ጦርነት ጀምሮ ለኢትዮጲያ ህዝብ ስፍር ቁጥር የሌላቸው በጎ ውለታወችን የዋሉት በ1906ዓም ላይ ከሐረር ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ እያሉ በድንገተኛ ህመም በ53 አመታቸው ህይወታቸው ያለፈው ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል ጉዴሳ ከሚኖሩበት ዘመን እና ህብረተሰብ ቀድመው የነቁ ስልጡን መሪ እንደነበሩ የተጻፈላቸውን የተለያዩ ጦማሮች አቅርቤ በተደጋጋሚ አስታውሼቸዋለሁ።

ከፊት ለፊት ያለውን ገደል ለመዝለል ወደ ኋላ መንደርደር አስፈላጊ ነውና እኛም አንዳንዴ ወደ ኋላ መለስ ቀለስ እያለን ለዚህ ዘመን ያበቁንን ያለፉትን አባቶችንን በክብር ማስታወሱ ይጠቀምናል እንጂ አይጎዳንም።

ንቁ ሰው ከታሪክ ፍቅርን እንጂ በቀልን አይወርስም።
Soutce: Eduardos-History-Page

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s