የስብሃት ገ/እግዚዓብሄር ስብከት. . .


mqdefaultስብሃት ገ/እግዚዓብሄር በአንድ ወቅት ከኢትዮ ቲዩብ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ይሄን ተናግሮ ነበር፡፡ ” ሁሌ በተቻለኝ መጠን የምሰብካት ስብከት አለችኝ የምሬን፤ በተቻለኝ መጠን ፤ ጠዋት ስትነቃ ተመስገን በል! በረከቶችህን ቁጠር ርዕሷ ነች ይህቺ ፡፡ ተመስገን በል ! ሞተህ ልታድር ትችል ነበራ ! ወይ ደግሞ ከዛ ከአልጋህ ወርደህ ስትቆም ተመስገን በል ! በሆነ ምክኒያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበር ፡፡ እ….ደግሞ ስትንጠራራ ደግሞ ደስ አይልም ? እ እ …ን.ዲ.ህ ስትል ደስስ አይልም ? መንጠራራትን የሰጠኸን እያልክ ተመስገን በል ? እያልክ ደግሞ ከዛ በፊት ሽንትህ ወጥሮህ ስትሸና የጠጣሀው ውሃ ሸንት ሆኖ መውጣቱ ፤ ይሄ የማናውቀው ተዓምር ውስጣችን መሰራቱ ፤ ተመስገን በል ! :: ከዛ ደግሞ ወጥተህ ስትሄድ መ..ን..ገ..ዱ. . ሁሉ ጤና ነው ፡፡ ታክሲው ፤ ሰዉ ፤ ምኑ ለማኙ መነኩሴው ፤ እሱን ስታይ ተመስገን በል ! ምክኒያቱስ ? ጄኔራል ሰጥ አርጋቸው የሚባሉ ጄኔራል ጨለማን ተገን አድርገው ፤ በታንክ ገብተው አገሩ ፀጥ ብሎ ቢቆይህስ ? ምን ታደርግ ነበር |? ጠላት አለኝ ይሆን እንዴ ? ተመልሼ ልግባ ? ደግሞ ተመልሶ ገባ ይሉኛል ፤ ምናምን ትል ነበር ፡ አገር ሰላም በመሆኑ ተመስገን በል ! እያልክ …. እያልክ ትሄዳለህ ፤ ቆማጣ ስታይ ውይ ረ…ስ..ቼ…ው መዓት ነው ፤ ሁልጊዜ ተመስገን በል ! ፤ ተመስገን በል ! አሁንም፡፡”

(ወዳጆቻችን እንዲያነቡት ሼር እናድርገው)

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s