ላጣሽ አቅም አጣሁ


ዓለማዊ ልቤ፤ ለበሰልሽ ዳባ
ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ፣የጠፋብኝ እንባ
ፊቴ ላይ ተገኘ
ላጣሽ አቅም አጣሁ፡፡

የሶምሶንን ገድል
ያላዛርን እድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብየ ነበር፤
ቄስ እንዳስተማረኝ
አንቺን አጣሁ ብየ፤ ማመኑ ቸገረኝ፡፡

ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፡፡

ልረሳሽ አልቻልኩም፤ ልረሳሽ እልና
ፊትሽን አትመሽ፣በየብስ በደመና
ከንፈርሽ ያውና
ፈገግታሽ ያውና
ውብ አይንሽ ያውና፡፡

(በእውቀቱ ሥዩም)

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s