ትንሽ ምክር ስለ ጤና . . .


የሰው ልጅ ስንዴን ከማምረቱ ፊት ገብስ በአውሮፓው አለም የህይወት መድህን ነበር፡፡ ፈረንጆቹ “ፋዘር ኦፍ ሜዲሲን” እያሉ የሚጠሩት ሂፖክራተስ “በየቀኑ ገብስ የተዘፈዘፈበትን ውሃ መጠጣት ጤናማ ህይዎትን መምራት እንደሚቻል አስገንዝቧል፡፡ የዚህ ሊቅ ምክር ከ2000 አመታ በኋላም ከየሰው ግንዛቤ ውስጥ አልተሰወረም ነበርና ሀኪምና የዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረው እንግሊዛዊው ኮምሬ “ዘ ኦክስፎርድ ሜዲካ አድቫይዘር” በተሰኘው መፅሃፍ ውስጥ የሚከተለውን የገብስ ውሃ አዘገጃጀት ጠቁሟል፡፡ “50 ግራም ድፍን የገብስ ፍሬ በግማሽ ሊትር ውሃ ውስጥ ለሁለት ሰዓታት ያህል ዘፍዝፈው ያቆና በማጥለያ ፍዎቹን ለይተው ያስወግዱ፡ ቀጥሎም ለማጣፈጥ በቂ ስኳርና መዓዛውን ለማሳመር የሎሚ ጭማቂ በውሃው ውስጥ ይጨምራሉ፡ ከዚያም ቀዝቃዛውን ውሃ ቢጠጡት ለታመመ ጉሮሮ ይበጃል፡ ወተትን ተክቶ ለምግብነት ሊውልም ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ትኩሳትን ያበርዳል፣ የኩላሊት ችግሮችን ይቀርፋል፡፡ ገብስ በቫይታሚን ኤ እና ቢ የበለጸገ ሲሆን ከ70-80 በመቶ የሚሆን ፕሮቲን ቅባ-ስታርትና ኢንዛይም አለው፡ የገብስ አሸት ሆርዴኒናንና አሚኖፌኖል የተሰኙ ጠቃሚ አልካላይድ በውስጡ ያካትታል፡፡
ምንጭ፡- ‹‹ዶክተር ለራሴ›› የባህል መድሃኒቶት መፅሃፍ

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s