የዕንቁው ታሪክ…


በአፍሪካ ምድር በእርካታና በደስታ የተሞላ ሕይዎት የሚመራ አንድ አርሶ አደር ነበር፡፡ የእርሶ አደሩ ስምም ሀፊዝ ይባል ነበር፡፡ ከቀናት በአንዱ ቀን አንድ አዋቂ የሆነ ሰው ወደ አርሶ አደሩ ቀርቦ ስለተወዳጁና አስደናቂው እንቁ ታሪክ ነገረው፡፡ የእጅህን መዳፍ ምታክል እንቁ ቢኖርህ አንድ ከተማ መግዛት ሚያስችል ሀብት ኖረህ ማለት ነው፡፡ ከእጅህ መዳፍ በለጥ ያለ እንቁ ኖረህ ማለትማ ሀገር መግዛት የሚያስችል ሀብት ኖረህ ማለት ነው፡፡ እያለ ካስረዳው በኋላ አዋቂው ሰውየ በዚህ አኳኋን የአርሶ አደሩን ልብ ሰቅሎ ተሰናበተው፡፡ በዚህች ቀን የሃሳብ መብሰልስሎት በልቡ ተጸንሳ ዕንቅልፍ እሚባል ነገር በአርሶ አደሩ ዓይን ሳይዞር ሌሊቱ ነጋ፡፡ በዛውም ላይ ዕንቁውን አጥብቆ ከመሻቱ የተነሳ ደስታ እያጣ ሲበሳጭ አደረ፡፡

በማግስቱ ያለውን የእርሻ መሬት ሸጦ ለቤተሰቦች ከሰጠ በኋላ ዕንቁ የሚገኝበትን ቦታ ለማሰስ በቁርጥ ውሳኔ ተነሳ፡፡ መላ የአፍሪካን ምድር አካለለ ነገር ግን አንዳችም አላገኘ፡፡ ወደ አውሮፓ አቅንቶም ስፔንን አዳረስ አሁንም አልተሳካም፡፡ እዚህ ደረጃ ሲደርስ ግን መንፈሱ እየተዳገመ፣ አካሉ እየጎሰቆለ የያዛት ገንዘብም ተመናምና አልቃ ነበርና በነገሮች ተሰላችቶና ተስፋ ቆርጦ ወደ ባርሴሎና ወንዝ እራሱን ወረወረ፡፡

የእርሻ ማሳውን የገዛው አዲሱ አርሶ አደር ከእርሻ ማሳው እግርጌ ጋር ተያይዞ ካለው ወንዝ አንድ ጠዋት ግመሎቹን ውሃ ሲያጠጣ የፀሐዩዋ ጨረር ከአንድ ድንጋይ ጋር ተጋጭቶ ሲመለስ ዓይኑ ላይ ቀስተዳመና ሰርቶ አንጸባረቀበት፡፡ በወቅቱ ገበሬው ሲመለከተው የብረት ቁራጭ መስሎት ነበር፡፡ አንስቶም ወደቤቱ ወሰደው፡፡ መጀመሪያውኑ ለስ እንቁ ተወዳጅነት ለአርሶ አደሩ ነግሮት የነበረው አዋቂ ሰው ዕንቁውን ባየ ግዜ ሀፊዝ ተመለሰ እንዴ ብሎ ጠየቀው፡፡

አዲሱ የእርሻ ማሳው ባለበት ግን ለምን ጠየከኝ ሲል ጠየቀው አዋቂውም ምክንያቱም እሱ ጋ ፊት ለፊት ለውን እንቁ ስለያሁ ነው አለው፡፡ አደለም ውበት ያላቸው ድንጋዮች ናቸው እኔ ነኝ ከወንዙ ዳር ለቅሜ ያመጣኋቸው ሲል መለሰ አዲሱ አርሶ አደር፡፡ ተያይዘውም የድንጋዮቹን ዕንቁ መሆናቸው ሊያስፈትሹ ሄዱ፡፡ አርሶ አደሩም የያዛቸው ድንጋዮች ዕንቁ መሆናቸውንና አዲስ የገሰዛው የእርሻ ማሳ በእንቁዎች የተሞላ መሆኑን ባወቀ ጊዜ እጅግም ደስ አለው፡፡

1. ለነገሮች ያለን ምልከታ ትክክል በሆነ ጊዜ በእንቁዎች ላይ እየተረማመድን እንደሆነ አንገነዘባለን፡፡ ሁሌም በሚያስብል ደረጃ መልካም አጋጣሚዎች እንደ ሀፊዝ አገር ሳናቆራርጥ እግራችን ስር አሉ፡፡ ልዩነቱ እነሱን መገንዘብ መቻሉ ላይ ነው፡፡

2. በእጃችን ላይ ያለውን ሳይሆን የሌለንን ለማየት መጓጓት በተለመደ አኳኋን የሰው ልጅ ስሜት ያመዝበታል፡፡

3. የመልካም አጋጣሚ እድሎች መረዳት እስካልቻልን ድረስ ትሩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ በራችንን ሲያንኳኩ እንደ እረብሻ ቆጥረነው ቅሬታ እያሰማን ሊሆን ይችላልና አንንቃ፡፡

4. አንዴ ያመለጠ መልካም አጋጣሚ (እድል) እራሱን ላይደግም ይችላል፡፡ ቀጣዩ በበለጠ ወይም ባለስ ሊከሰት ይችላል አንጅ፡፡

(‪qouted from facebook/https://www.facebook.com/misganaw.gishen/)

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s