እንደገና መወለድ


ንስር አሞራ እስከ ሰባ ዓመት በሕይዎት የመኖር ጸጋ ተሠጦታል፡፡ ነገር ግን ይህን 70 ዓመት የዕድሜ ፀጋን አጣጥሞ ለመኖር አርባኛ ዓመቱ ላይ በሕይዎቱ ወሳኝ የሚባል ውሳኔን ማሳለፍ ይጠበቅበታል፡፡ ይኸውም ንስሩ አርባኛ ዓመት ዕድሜው ላይ እነዛ እረዥምና እንደልብ የሚተጣጠፉት ጥፍሮቹ እንደ እነጨት ይገራሉ፡፡ ስል የነበረው ማቁርቱም ወደ አንገቱ ይታጠፍና ምግቡን አንድኖ እንዳይዝ ያግደዋል፡፡ የገረጀፉት ላባዎቹም ከደረቱ ላይ ተጣብቀው የመብረር ስራውን አስቸጋሪ ያደርጉበታል፡፡ በዚህ ወቅት ንስሩ ሁለት ወሳኝ አማራጮች ይጠብቁታል፡፡ አንድም ሞትን አሜን ብሎ መቀበል ወይም ደግሞ አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት ሚፈጅን ፈታኝ የለውጥ ሂደት ማካሄድን፡፡ በለውጡ ሂደት ለማለፍ ከወሰነ ቀጣዮችን ተግባራት መፈጸም ይጀምራል፡፡ በመጀመሪያ ንስሩ ከፍ ብሎ ከወጣ ተራራ አለት ላይ ይቀመጥና የታጠፈውን ማንቁርቱንና ጥፍሮቹን ከአለቱ ጋር ደጋግሞ በመምታት ወልቀው እንዲወድቅ ያደርጋል፡፡

የገረረውና የታጠፈውን ማንቁርት እንዲሁም ጥፍሮቹን አውልቆ ከጣለ በኋላ ከስር የወጣው ሙሽራ ማንቁርትና ጥፍር እስኪጠነክር ድረስ ለቀናቶች ይታገሰዋል፡፡ ማቁርቱና ጥፍሮቹ ከጠነከሩ በኋላ ቀጣይ የሚጠብቀው ተግባር የደረቁትና ከደረቱ ጋር ተጣብቀው ከመብረር ያገዱተን ላባዎች እየነጨ በማራገፍ በአዲስ እንዲተኩ ማድረግ ነው፡፡ ይህን እልህ አስጨራሽና አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት ወይም አመስት ወራት የፈጀውን የለውጥ ጉዞ ካካሄደ በኋላ ዳግም ውልደቱን የሚያበስር ቀጣይ ሰላሳዎቹን ዓመታትም በትኩስ ኃይል መኖር የሚያስችል ለውጥ አደረገ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታም የዳግም ውልደቱን በረራ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ይጀምራል፡፡

ብዙውን ጊዜ አዳዲስ ክስተቶችን ተገንዝቦና ተላምዶ በለውጡ ተጠቃሚ ለመሆን እልህ አስጨራሹን ለውጥ ሂደትን መታገስ ይጠይቃል፡፡ የቆዩና ያፈጁ አስተሳሰቦችን ከእሳቤ ውስጥ ማስወገድ፡፡ ከቆዩና ኋላ ቀር ልማዶች እራስን ነፃ ማድረግ አሁን የተፈጠረልንን ጥሩ እድል ለመተቀም ያስችላል፡፡

ምንጭ፡ Story of the Eagle

Advertisements

please enter a message

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s