አስተማሪው ናስሩዲን. . .


pic-nesrudin

pic-nesrudin


ጥቂት ወጣቶች ተሰብስበው ወደ ሙላ ናስሩዲን ቤት መጡና መምህራቸው ይሆን ዘንድ ጠየቁት። ናስሩዲንም በሀሳቡ ተስማማና ተማሪዎቹ ወደ ሱፊዎች ማረፊያ ዘንድ እንዲከተሉት ነገራቸው። በዚህም መሰረት ናስሩዲን ፊቱን አዙሮ አህያው ላይ ወጣና ጉዞ ተጀመረ። የከተማው ነዋሪ በሙሉ በናስሩዲን ሞኝነት ተገርሞ መሳቅ ጀመረ። ህዝቡ ተከታዮቹን እንደ ጅል ቆጥረው ሲያፌዙባቸው ቁጥራቸው ተመናመነ። ከሱፊ ማረፊያው ዘንድ ሲደርሱ የቀሩት የናስሩዲን ተከታዮች ቁጥራቸው በጣም ትንሽ ነበር። ከነዚህ አንዱ ናስሩዲንን እንዲህ ጠየቀው፦
”ናስሩዲን ሆይ!ለምንድነው በአህያዋ ላይ ፊትህን አዙረህ የተቀመጥከው?“
ራስሩዲንም ሲመልስ፦
“ተማሪዎች ከአስተማሪያቸው ፊት ቀድመው እንዲሄዱ መፍቀድ አግባብ አይደለም፤ እኔም በበኩሌ ለተማሪዎቼ ጀርባዬን ሰጥቼ መሄድ አልችልም”
ከዚህ አጭር ታሪክ ሶስት አበይት ነገሮችን መማር እንችላለን

 • ናስሩዲን ተማሪዎቹን ለማስተማር ከተለመደው ወጣ ያለ መንገድን በመከተል በዚያውም የተማሪዎቹን ለራስ ያላቸውን
  ታማኝነትና ቆራጥነት እንዲሁም በራስ መተማመን ይገመግማል
  — አንድ አስተማሪ የሚሄድበትን መንገድ የሚያውቅ፡ አትኩሮቱ ግን ተማሪዎቹ ላይ ሊሆን እንደሚገባ ይጠቁማል
  — በተማሪ እና በአስተማሪ መሀል እርስ በእርስ መኖር ስላለበት መከባበርም ያስታውሳል
 • Advertisements

  please enter a message

  Please log in using one of these methods to post your comment:

  WordPress.com Logo

  You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

  Google+ photo

  You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

  Twitter picture

  You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

  Facebook photo

  You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

  w

  Connecting to %s