ምንሊክ አደባባይ 1930/


statute of Menilik

በ1937 በጥሊያን መትረየስ በግፍ የወደቁት ጀግናው መለኩሴ ከፍቼ ምድር የሚጠለቁት አቡነ ጴጥሮስ በዚህ ግርግር መሀከል እንደነበሩ ጥሊያኑ ታሪክ ጦማሪ Angelo Del’boca ጽፎታል። ዘውድ ከጫኑ አመት ያልሞላቸው ጃንሆይም በቦታው ተገኝተው ሐውልቱን መርቀው ከገለጡ በኋላ ተሰብስቦ ለነበረው ሕዝብ እና ለውጭ አገር እንግዶች ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር ላይ አጤ ምንሊክ እድሜቸውን በሙሉ ለአገራቸው የኖሩ ታላቅ የኢትዮጲያ ልጅ እንደነበሩ መስክረዋል።

በየትኛው አገር ወይም ክፍለ አለም, በቀጥታም ይሁን በእጅ አዙር የገዛ ህዝቡን ያልበደለ, ያልገደለ አንዱን እጠቅማለሁ ብሎ ሌላውን ያልጎዳ አንድም የአገር ገዢ የለም ስለዚህ እኛም በድሮ በሬ ከታረሰው እርሻ ክፉ እና ደጉን ተመርን ወደፊት መጓዝ ነው እንጂ ቅራኔ እና በቀል በልቦና መቋጠር ግን ቂልነት ነው።

እንደ ታሪክ መንፈስን የሚያድስ ምንም አይነት እውንታ የለም ታዲያ የትላንቱን እያሰቡ ከትላንቱ እየተማሩ ዛሬን መኖር የአዋቂ ሰው ንቃት ህሊና ሲሆን ያልነቃው ደግሞ በተዘመረበት እያጨበጨበ በነዱት እየተነዳ, የውሀ ላይ ኩበት ሆኖ ይኖራል።Eduardos-History-Page

please enter a message